Fana: At a Speed of Life!

የህልውና ማስከበሩ በልማት ሊደገፍ እንደሚገባ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የህልውና ማስከበሩ በልማት ሊደገፍ ይገባል ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ።

ዶክተር ይልቃል በክልሉ ሦስት ዞኖች እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ልማት ተግባራት ጉብኝት ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ህልውናን ለማስከበር የሚደረገው ትግል በልማት ሊደገፍ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዝናብ አጠር አካባቢዎች ሳይቀር ስንዴ ማልማት መቻላቸውን አስታውሰዋል፡፡

ግብርናውን ወደ ሜካናይዜሽን ለማሻገር እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው÷ በዘርፉ የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል፡፡

ስንዴን ወደ ውጭ ለመላክ እንደ ሀገር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካት ባለ ድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በበላይነህ ዘለዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.