የሀገር ውስጥ ዜና

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ለ4ኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገ

By Tamrat Bishaw

October 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ለ4ኛ ጊዜ የሰንጋ እና የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሃርቢ ቡህ ህዝቡ ሁልጊዜም ለሃገር ክብር ከሚዋደቀው የኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን በደጀንነት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ከ65 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ያስታወሱት ምክትል ከንቲባው÷ አንድነታችንን ጠብቀን ለሀገር ሉዓላዊነት ዘብ የቆመውን መከላከያ ሰራዊት ልንደግፈው ይገባል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ አትሌት ድንቅነህ ሶዳ 100 ሺህ ብር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

በአትሌቲክሱ ዘርፍ በዓለም አደባባይ ድል አድርጎ ሰንደቅን በኩራት ማውለብለብ የሚቻለው ሀገር ሲኖር ነው ያለው አትሌት ድንቅነህ ሶዳ፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ህልውና ምክንያት ስለሆነ ልናከብረው እና ልንደግፈው ይገባል ብሏል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ዘላለም ፈተና ሁሉም ዜጋ በየተሰማራበት ለሀገር መከበር እያደረገ ላለው አስተዋፅጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡