አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 298 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 298 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ ።
በምረቃው ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና እና የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል ።
ከዛሬ ተመራቂዎች መካከል 184 ወንዶች ሲሆኑ 114 ደግሞ ሴቶች ናቸው ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ኮሌጅ የህክምና ተማሪዎችን አስተምሮ ሲያስመርቅ ዘንድሮ ለ51 ጊዜ መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።