Fana: At a Speed of Life!

አቃቂ የኢንዱስትሪ መገኛ ክፍለ ከተማ እንደመሆኑ የህዝብን ችግር ለመፍታት ትልቅ እድል ያለው ክፍለ ከተማ ነው- አቶ ጃንጥራር አባይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የኢንዱስትሪ መገኛ ክፍለ ከተማ እንደመሆኑ የህዝብን ችግር ለመፍታት ትልቅ እድል ያለው ክፍለ ከተማ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከህዝቡ ጋር በትብብር የሚፈፀሙ የ90 ቀን ሰው ተኮር ኘሮጀክቶች እቅድ ይፋ ተደርጓል፡፡

የሰው ተኮር ኘርጀክቱ ዝርዝር ተግባራት ላይ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ እና የክፍለ ከተማው የነዋሪ ተወካዮችና ባለ ሀብቶች በተገኙበት ምክክር ተደርጓል።

አቶ ጃንጥራር በምክክር መድረኩ እንደገለጹት÷በክፍለ ከተማው በ90 ቀናት ከሚሰሩት ኘሮጀክቶች መካከል የህፃናት አዕምሯዊና አካላዊ ማበልፀጊያ ማዕከላት፣ አደባባዮችና የመንገድ አካፋዮች የመብራት የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያዎች ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የአካባቢ ጥበቃ ልማቶች፣  የምገባ ማዕከላት፣ የኮምዩኒቲ ፖሊስ  ጣቢያዎች፣ ሁለገብ የተቀናጀ የከተማ ግብርና፣ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ግንባታ ፕሮጀክቶች ዋናዋና ግቦች ናቸው ብለዋል።

ባለሀብቶችን በማስተባበር የአቅመ ደካማ ቤቶች አድሳት እንደሚሰራም ጠቅሰው÷የበጋ ወራት ለሚታደሱና ለሚገነቡ ቤቶች ምቹ ወቅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባለሃብቱም  በወሰደው መሬት ልክ ወደ ልማት መግባት እንዳለበት ማሳሰባቸውንና የታቅደው እንዲፈፀም አመራሩ በትኩረት መንቀሳቀስ እንዳለበት  አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሌብነትን መታገል፣ የኑሮ ውድነት የሚያቃልሉ ተግባራትን መፈፀም፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል በ90 ቀን እቅዱ የሚሰሩ ናቸው ያሉት ደግሞ አዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት  ኮሚሽነር አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.