Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በረቂቅ አጀንዳዎች ማሰባሰብ ሥርዓት ላይ ከምስራቅ አጎራባች ክልሎችና ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በረቂቅ አጀንዳዎቹ ማሰባሰብ ሥርዓት ላይ ከምስራቅ አጎራባች ክልሎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በጅግጅጋ ከተማ እየመከረ ነው፡፡

በውይይቱ ከሶማሌ ክልል 11ዱ ዞኖች፣ ከተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች እንዲሁም ከሐረሪ ክልልና ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከሀገር ሽማግሌዎች የተወጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ዲሪር÷ የመድረኩ ዋና አላማ በቀጣይ ኮምሽኑ ለሚያካሂደው የትግበራ ሂደት ምዕራፍ በሀገራዊ ምክክር መድረኩ ላይ አካታችነት ፣ግልፀኝነትና አሳታፊነት እንዲሁም ተአማኒነትን የጎላ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

በምክክር መድረኩ ስለ ኮሚሽኑ አሰራርና ሂደቶች ላይ ለተሳታፊዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ÷ከተሳታፊዎችም የግብዓት ሀሳብና አስተያየት መሰጠቱን ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መድረኩ ነገም የሚቀጥል ሲሆን÷ በተለያዩ የኮምሽኑ ሰነዶችና ነጥቦች ላይ እንደሚወያይ ታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.