Fana: At a Speed of Life!

መንግስት መጪው ትውልድን በመስራት ሀገርን ለማሻገር ስራ ትኩረት ሰጥቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ትውልድን በመስራት ሀገር ለማሻገር ስራ ትኩረት ሰጥቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሸገርን ማስዋብ ምዕራፍ ሁለት አካል የሆነውን የወዳጅነት አደባባይ ምዕራፍ ሁለት መርቀው ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ ወቅት ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ ቁጥሩ ከፍ ያለ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እንዳሏት ገልጸው ፥ ከተጨማሪ ግንባታ ይልቅ የቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲገነቡ መደረጉን አንስተዋል።

በዚህም ሰው ለሚሰራባቸው ነገሮች ቅድሚያ ተሰጥቶ ተሰርቷል እየተሰራም ይገኛል ነው ያሉት።

የወዳጅነት ምዕራፍ ሁለት ግንባታም ህፃናት የሚጫወቱባቸውና ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ፕሮጀክቶችን ያካተተ እንደሆነም አንስተዋል።

ህፃናት ላይ መስራት የነገ ሀገርን የመገንባት አካል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በተያያዘ 9 ሚሊየን ህፃናትን መመገብ እንደተቻለም ገልጸዋል።

በፕሮጀክቱ የተካተቱ መጫወቻዎች ህፃናት የአካል ብቃት እየሰሩ አዕምሯቸውን የሚያበለፅጉባቸው እንደሆኑም ነው ያብራሩት።

ፕሮጀክቱ ለህጻናትና ታዳጊዎች ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የእድሜ ክልል ለመገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችና ጎብኚዎች የሚሆን ስፍራ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሌሎች አካባቢዎችም ሊደገም ይገባልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

የወዳጅነት ምዕራፍ ሁለት ለመጪው አንድ ሳምንት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በነፃ መጎብኘት እንደሚችሉም ነው ያስታወቁት፡፡

አሁን የሚታዩ ችግሮች ልጆች ላይ ያለመስራት ውጤት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለነገ ሀገር ግንባታ መሰረት የሚጥሉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.