የሀገር ውስጥ ዜና

ከሰሜን ወሎና አካባቢው በአሸባሪው ህወሓት ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው

By Tamrat Bishaw

October 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአላማጣ፣ ቆቦ፣ ዋጃ እና ባላ እንዲሁም ከሌሎች አካባቢዎች በአሸባሪው ህወሓት ተፈናቅለው በጃራ መጠለያ ካምፕ የነበሩ 30 ሺህ 400 ወገኖች ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል፡፡

ሃብትና ንብረታቸው በሽብር ቡድኑ በመዘረፉ መንግሥት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ ዓለሙ ይመር ÷ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የተራድዖ ድርጅቶች ጭምር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን በትኩረት እየሠራ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።