Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ትክክለኛው አቅጣጫ አፍሪካዊ መፍትሔ ነው- አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ትክክለኛው አቅጣጫ አፍሪካዊ መፍትሔ መስጠት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተናገሩ፡፡

እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባኤ ላይ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል።

አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በመድረኩላይ እንደገለጹት÷ አፍሪካውያን ችግሮችን ለመፍታት በሰላም ግንባታ እና በፀጥታ ጉዳዮች በርካታ አቅም አላቸው፡፡

አህጉሩን በቀጣይ የሚመሩት ወጣቶች የእርስ በእርስ ግንኘነትን በማጠናከር ለጋራ ውጤት መስራት አለባቸው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ አህጉር የምትወከለበት ስርዓት በድጋሚ መታየት እንዳለበትም ገልፀዋል።

በውይይቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብረሃ የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ እና ታሪክ በሚል የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እንድሪስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ÷ በአፍሪካ ለሚፈጠሩ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እንዲሁም ማህበራዊ ችግሮች ብቸኛው መፍትሔ አፍሪካውያን ችግሮችን የሚፈቱበት መንግድ የራሳቸው አገር በቀል እውቀት መሆን አለበት ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.