የኢፌዲሪ መንግሥት በሞቃዲሾ በተፈጸሙ ጥቃቶች በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መንግሥት በሞቃዲሾ በተፈጸሙ ዘግናኝ ጥቃቶች በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል፡፡
የኢፌዲሪ መንግሥት÷ ለሟች ቤተሰቦች እና ለተጎጂዎች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
ይህ አስፀያፊ ድርጊት አሸባሪ ቡድኑ ተስፋ እየቆረጠ መምጣቱን አመላካች መሆኑን ነው መንግሥት የገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥትም ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ እና በዚህ የፈተና ወቅት ከሶማሊያ መንግስት እና ሕዝብ ጎን መሆኑን በአጽንኦት ገልጿል፡፡