ኮሮናቫይረስ

በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘው ሳንሼንግ ፋርማቲካል በቀን 24 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘር ማምረት ጀመረ

By Tibebu Kebede

March 24, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዱከም የሚገኘው ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘው ሳንሼንግ ፋርማቲካል በቀን 24 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘር ማምረት ጀመረ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ አበባየሁ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘው ሳንሼንግ ፋርማቲካል የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ማምረት ላይ ትኩረት የሚያደርግ አዲስ ክፍል መክፈቱን ገልፀዋል።