Fana: At a Speed of Life!

በዶክተር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልዑክ በሰሜን ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልዑክ በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኘ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በወረዳው ገርባ ቀበሌ በ1 ሺህ 379 ሔክታር ላይ የለማ የስንዴ ማሳን ነው የጎበኙት፡፡

በወረዳው11 ሺህ 375 ሔክታር በኩታ ገጠም የለማ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 500 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷ የአርሶ አደሩ ሰብልና ታታሪነትበምግብ ራስን መቻልን እንዲሁም ስንዴን ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደምንችል ማሳያ ነው።

ይህ ውጤት ለአርሶ አደሩ የማዳበሪያ ግዥ ድጎማ በማድረግ ጭምር መገኘቱንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ስንዴ መለመን ታሪክ ሆኗል ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ÷ የታፈረችና የተከበረች ሀገር እንድትኖረን ድህነትን ማሽነፍ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን በተያዘው የምርት ዘመን ከ146 ሺህ ሔክታር በላይ በስንዴ ሰብል የተሸፈነ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 54 ሺህ ሔክታሩ በኩታገጠም የታረሰ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ተናግረዋል።

በክላስተር ከለማው ስንዴ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ነው የተነሳው፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኃይለማርያም ከፋለ እንደገለጹት÷ በተያዘው በጀት ዓመት በክልሉ የመስኖ ስንዴን ጨምሮ 40 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ይጠበቃል፡፡

በአላዩ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.