የሀገር ውስጥ ዜና

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰሩ 38 ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ተላለፉ

By Meseret Awoke

October 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ከተማ በ11 ሚሊየን ብር ወጪ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተሰርተው የተጠናቀቁ 38 ቤቶች ለአቅመደካሞች ተላልፈዋል፡፡

የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ አዳነ ተ/ጊዮርጊስ በዚህ ወቅት ፥ ቤቶቹ ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ ድጋፍና ክትትል ሲደረግ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡

የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ሶቦቃ በበኩላቸው ፥ ካለፈው ዓመት ልምድ በመነሳት የዚህ ዓመት አፈጻጸማችንን የተሻለ አድርገናል ብለዋል፡፡

ለእነዚህ ወገኖች ለሦስት ወራት የሚሆን ቀለብ፣ አልጋ፣ ብርድልብስና ለእያንዳንዳቸው 2 ሺህ ብር እንደተሰጣቸውም አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወካይ ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ በበኩላቸው ፥“አንድነታችንን ካጠናከርን በመተሳሰብና በመደጋገፍ ችግሮቻችንን መቅረፍ እንችላለን፣ ለዚህ ደግሞ ይህ ሥራ ምስክር ነው” ብለዋል፡፡

የቤቶቹን ቁልፍ የተረከቡ ተጠቃሚዎች፥ የተሰጣቸው ቤት በመኖሪያ ቤት እጦት ሲደርስባቸው የነበረውን ችግር እንደሚያቃልልላቸው መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!