አሜሪካ ያጋጣሟት ውስጣዊ ችግሮች ከቁጥጥር ውጭ እየሆኑ መምጣታቸውን የህዝብ አስተያየት አመላከተ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ያጋጣሟት ውስጣዊ ችግሮች ከቁጥጥር ውጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ከህዝብ የተሰበሰበ አስተያየት አመላከተ።
ሲ ቢ ኤስ አሜሪካ አሁን ላይ ያለችበትን ሁኔታ በተመለከተ የህዝብ አስተያየት ሰብስቧል።
በሀገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት እና የነዳጅ ዋጋ መጨመር በሀገሪቱ የተከሰቱ ውስጣዊ ችግሮች ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል ብለዋል አስተያየት ሰጭዎቹ።
የህዝብ አስተያየቱ አስተያየት እንደሚያመላክተው 79 በመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን አሁን ላይ “ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ናቸው” ብለው ያምናሉ፡፡
21 በመቶዎቹ ደግሞ ሁሉ ነገር ከቁጥጥር ውጭ አይደለም ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ነገሮች ከፍተዋል ካሉት ውስጥ 73 በመቶዎቹ ችግሮች ከቀን ወደ ቀን እየከፉ ነው የሚል ሃሳብ አላቸው።
በተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ከተሳተፉት መካከል ከዴሞክራት 48 በመቶ፣ ከሪፐብሊካን 12 በመቶ እንዲሁም 18 በመቶ የሚሆኑት ገለልተኛ አካላት በአሜሪካ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በአስተያየት መስጫው 56 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን አስተዳደር ሲቃወሙ፥ 44 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የባይደንን አስተዳደር አፈፃፀም ደግፈዋል።
በቅርብ ጊዜ በሬውተርስ የተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት ደግሞ የባይደን አስተዳደርን የተቀባይነት ደረጃ ወደ 39 በመቶ መቀነሱን ያመላክታል።
የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሚካሄድ ሲ ቢ ኤስን ጠቅሶ ፕረስ ቲቪ ዘግቧል፡፡