Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መንግስት በህንድ በድልድይ መደርመስ አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በህንድ ጉጃራት ግዛት በደረሰ የድልድይ መደርመስ አደጋ ህይወታቸው ባለፈ ዜጎች የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡
 
የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ በሕንድ ጉጃራት ግዛት ትናንት በደረሰ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድይ መደርመስ አደጋ የበርካታ ዜጎች ሕይወት እንዳለፈ መረዳቱን አንስቷል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም አደጋው በበርካታ ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት ማድረሱ ነው የተመላከተው፡፡
 
የኢትዮጵያ መንግስት በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ÷ለህንድ መንግስት እና ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
 
በአደጋው የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችም በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.