Fana: At a Speed of Life!

በ50 ሚሊየን ዶላር እየተገነባ የሚገኘው የኢ-ኮሜርስ የጭነት አገልግሎት ማዕከል በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚሊየን ዶላር እያስገነባ ያለው ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ የጭነት አገልግሎት ማዕከል በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር አስታወቀ።

በዓለም የኢ-ኮሜርስ ንግድ እየተስፋፋ መሆኑን ተከትሎ አየር መንገዱ ተወዳዳሪነቱን ለማስቀጠል የካርጎ አገልግሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

የአየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ እንደገለጹት÷አየር መንገዱ በካርጎ አገልግሎት ከአፍሪካ ትልቁና በዓለም ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ ዘመናዊ አሰራርን ይከተላል።

አዲሱን የካርጎ አገልግሎት ማዕከል እውን ለማድረግ እውቀትና የአሰራር ስርዓት በአግባቡ ተዘርግቶለት ሊሰራ እንደሚገባው የቦርድ ሰብሳቢው ጠቁመዋል፡፡

አሰራሩ ከዚህ ቀደም ከነበረው የካርጎ አገልግሎት በእጅጉ የሚለይ መሆኑን ጠቅሰው÷ ዕቃ ከውጭ ተጭኖ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ይወስድ የነበረውን እስከ 7 ቀን በአዲሱ አሰራር እንደሚቀረፍ ተናግረዋል።

በአየር መንገዱ የካርጎና ሎጀስቲክስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቤል አለሙ በበኩላቸው÷የኢ-ኮሜርስ ማዕከሉ በመጪው የፈረንጆቹ 2023 አጋማሽ ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በዓለም ላይ በፍጥነት እየተሰራበት ያለውን ፈጣን የካርጎ አሰራር በመከተል እንደሚሰራ መገለጹንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሀገር ውስጥ ገቢና ወጪ ዕቃዎች በዚሁ አሰራር እንዲታገዙ የሚደረግ መሆኑም በመድኩ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.