Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የጥቁር ባህርን “የእህል ምርት መተላለፊያ” መስመር ዘጋች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ዩክሬን የእህል ምርቷን በጥቁር ባህር ወደብ ወደ ዓለም ገበያ የምትልክበትን መስመር በድጋሚ መዝጋቷን አስታወቀች፡፡

ሞስኮ የእህል ማስተለላለፊያ መስመሩን በድጋሜ የዘጋጀው ዩክሬን “ለእልህ ምርት መተላለፊያ” የተፈቀደውን መስመር ለወታደራዊ እንቀስቃሴ አገልግሎት እያዋለችው ነው በሚል ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በጥቁር ባህር ወደብ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የሩሲያ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የሩሲያ ጦር አስታውቋል።

መርከቦቹ በጥቁር ባህር ቅኝት የሚያደርጉ ሲሆን፥ በተፈጸመቫቸው ጥቃት ሳቢያ ለጉዳት መዳረጋቸው ነው የተነገረው።

ውሳኔውን ተከትሎም በኮሪደሩ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ስለሆነም ዩክሬን የፈጠረችው ችግር መፍትሄ እስከሚሰጠው ድረስ የእህል ማስተላለፊያ መስመሩ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ ነው የተገለጸው፡፡

በቅርቡ ዩክሬን የእህል ምርት ከጥቁር ባህር ወደቦች ወደ ዓለም ገበያ እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት በተመድ አደራዳሪነት ከሩሲያና ጋር መፈራረሟ ይታወሳል፡፡

የሩሲያ ባለስልጣናት ዩክሬን ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተፈራረመችውን ስምምነት እንድታከብር ማሳሰባቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.