Fana: At a Speed of Life!

ሊግ ኩባንያው በ5ኛ ሳምንት በተስተዋሉ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ በ5ኛ ሳምንት በተስተዋሉ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡

የኩባንያው ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ባደረገው ስብሰባ በ5ኛ ሳምንት በተደረጉ ውድድሮች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የሥነ ምግባር ሪፖርት በመመርመር የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በተጫዋቾች ደረጃ ኩሊባሊ ከድር (ፋሲል ከነማ) በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ 1 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ 1 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኗል።

በክለቦችድ ደግሞ  መቻል ፣ ድሬደዋ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ፋሲል ከነማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ አምስት እና ከዛ በላይ ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተመለከቱ በመሆኑ በእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል፡፡

እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ደጋፊዎቹ በፈጸሙት ጥፋት ክለቡ 50 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኖበታል፡፡

ነቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ፣ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ 18 ጎሎች በ17 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል።

በሳምንቱ 58 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች ቢጫ ካርድ ሲመለከቱ አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

የሊጉ 6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በድሬዳዋ የሚደረጉ መሆኑን ከቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.