በመዲናዋ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ በአፍ መፍቻ ቋንቋ አጠቃቀምና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
ውይይቱን እያካሄዱ የሚገኙት÷ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ የትምህርትና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እና ባለድርሻ አካላት ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ ባደረጉት ንግግር ÷ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ማስተማሪያ ቋንቋዎች በመተርጎም የትምህርት ባለሙያዎችን የመለየት ሥራ ተሠርቷል ብለዋል፡፡
በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ የመማሪያ መጻሕፍት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ሦስት ሚሊየን የመማሪያ መጻሕፍት እደተዘጋጀ እና እስካሁንም 1 ነጥብ 2 ሚሊየኑ እንደተሠራጨ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርትና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት÷ የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት አተገባበር ክፍተት አለበት፡፡
ለአብነት÷ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ዕውቅና ውጭ በሆኑ መጻሕፍት ማስተማር፣ የሥርዓተ ትምህርቱን አይነቶች መቀነስ ፣ ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ውጭ ባለ ቋንቋ ማስተማርና ሌሎች ክፍተቶች መስተዋላቸውን አብራርተዋል፡፡
በመሳፍንት እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!