በኦሮሚያ ክልል የበጋ ስንዴ ልማት መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ወልመራ ወረዳ የበጋ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሄደ፡፡
ዛሬ የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ክልል አቀፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አበራ ወርቁ እንደገለጹት÷ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት 50 ሔክታር በበጋ መስኖ ይሸፈናል፡፡
በወልመራ ወረዳ ደግሞ 350 ሔክታር መሬት የበጋ ስንዴ በኩታገጠም ያለመ መርሐ ግብር ዛሬ በይ ፋ ተጀምሯል ብለዋል፡፡
በክልል ደረጃም አንድ ሚሊየን ሔክታር በበጋ ስንዴ እንደሚሸፈን እና ከዚህም 40 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!