በዘንድሮው መኸር የሚገኘው የስንዴ ምርት ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ያበረክታል- አቶ አሻድሊ ሀሰን
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዘንድሮው መኸር የሚገኘው የስንዴ ምርት በቀጣይ ዘርን በራስ አቅም ከመሸፈን አልፎ ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እደሚያበረክት አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአሶሳ ዞን አብራሞ ወረዳ እየለማ የሚገኘውን የስንዴና አኩሪ አተር ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
አቶ አሻድሊ በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት÷ ባለፉት ዓመታት ስንዴ ያልተመረተባቸው አካባቢዎች በዘንድሮው የመኸር ወቅት ስንዴ ወደ ማምረት ገብተዋል፡፡
በመኸር ወቅት እየለማ የሚገኘው ስንዴ በክልሉ ስንዴን በስፋት የማምረት አቅም እንዳለ ማሳያ ነው ማለታቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተያዘው የመኸር ወቅት ከ346 ሺህ በላይ ኩንታል የስንዴ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱም ተገልጿል፡፡
በመኸር ወቅት የሚገኘው የስንዴ ምርት ኢትዮጵያ ስንዴን ወደውጭ ለመላክ የያዘችውን እቅድ ለማሳካት እንደሚያግዝ እና የስንዴ ዘር ፍላጎትን በራስ አቅም እንደሚሸፍን አቶ አሻድሊ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በበጋ ወቅት ከ11 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!