የሀገር ውስጥ ዜና

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እና ፓወር ፎር ኦል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

By Feven Bishaw

November 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከፓወር ፎር ኦል ጋር በቴክኒክ ድጋፍና አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት÷ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ እና የፓወር ፎር ኦል መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ክርስቲና ስኬርካ ናቸው፡፡

ፓወር ፎር ኦል ለሚጀምረው አዲስ ፕሮጀክት የሦስት ዓመት የቴክኒክ ድጋፍና የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

ኢንጂነር አይሻ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ÷ የዘርፉን አቅም ለመገንባትና የመስኖ ግብርናን ለማሳደግ ስምምነቱ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

የመስኖ መሰረተ ልማቶች ደረጃቸውን ጠብቀው ይገነባሉ ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ክርስቲና ስኬርካ በበኩላቸው ስምምነቱ÷ በዲዝል ውሃ ፓምፕ የሚጠቀሙ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ወደ ታዳሽ የኃይል ምንጭ ተጠቃሚነት ያሸጋግራል ብለዋል፡፡