Fana: At a Speed of Life!

አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ ከሞሮኮ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ ከሞሮኮው አፈጉባዔ ራችድ ታልቢ አል-አላሚን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው÷ ኢትዮጵያና ሞሮኮ በፓርላሜንታዊ፣ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና በባህል ልውውጥ ላይ በጋራ መስራት እንዳለባቸው መክረዋል፡፡

አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ÷ ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ጠንካራ ግንኙነት እና ተመሳሳይ ባህል ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸው የሚያደርጉት የባህል ልውውጥ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የንግዱን ማህበረሰብ የእርስበርስ ግንኙነት ማጠናከር እንዳለባቸውም ነው አፈጉባዔ ታገሰ የገለጹት፡፡

በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በጋራ አቋምና በትብብር መንፈስ በጋራ እንደሚሠሩም ማረጋጋጣቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

አፈጉባዔ ራችድ ታልቢ አል-አላሚ ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ትልቅ ታሪክና ባህል ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ጠቁመው÷ በቀጣይም የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በጋራ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.