Fana: At a Speed of Life!

ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች የመከላከያ ሚኒስቴርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ለወጣቶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴር ልዩ ረዳት እና ስትራቴጂክ ጉዳዮች አማካሪ ታዬ ሙሉጌታ ባስጎበኙበት ወቅት÷ አዲሱ ሕንጻ በአራት ማዕዘን ቅርጽ መገንባቱን እና የጋሻና ጦር ቅርጽ መያዙን አብራርተዋል፡፡

ሕንጻው ዘመኑን የሚመጥን እና በውስጡም በርካታ ሥራዎች መሥራት የሚያስችሉ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት አስረድተዋል፡፡

ወጣቶቹ በሰጡት አስተያየት የመከላከያ ሚኒስቴር ሕንጻ ባህልና ታሪክን አቅፎ የያዘ እና ውጫዊ ገጽታውም እንዳስደሰታቸው መናገራቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.