Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ በ”ጂኦስፓሻል” ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ በ”ጂኦስፓሻል “ዘርፍ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫለቱ ሳኒ የተመራ የልኡካን ቡድን በኪንቴክስ ደቡብ ኮሪያ በፈረንጆቹ ከህዳር 2 እስከ 4 ለሚካሄደው “ስማርት ጂኦስፓሻል ኤክስፖ 2022 ” ላይ ለመታደም ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል፡፡

ለልዑኩም የደቡብ ኮሪያ የመሬት መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ሚኒስትር ሂ ርዮንግ እና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ አቀባበል አድረገውላቸዋል፡፡

በሌላ በኩል በተለያዩ እንደ ሀገር በሚተገበሩ የዘርፉ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማድረግ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.