Fana: At a Speed of Life!

“ኢትዮጵያን ከባዕዳን ጣልቃ ገብነት ለመታደግ ያለ ልዩነት እንቆማለን” – ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፖለቲካ ልዩነት በላይ የሆነችውን ኢትዮጵያ ከባዕዳን ጣልቃ ገብነት ለመታደግ ያለ ልዩነት እንደሚቆሙ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ፡፡

አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማዳን እየተደረጉ ያሉ ጣልቃ የመግባት ፍላጎቶች እውነታን የካዱ እንደሆኑም አንስተዋል፡፡

የባዕዳኑ ፍላጎት የኢትዮጵያን ኅልውና አደጋ ላይ መጣል እንደሆነ በተግባር ማሳየታቸውንም አክለዋል፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአብን ምክትል ሊቀመንበር መልካሙ ሹምዬ ÷ጣልቃ የመግባት ፍላጎቶቹ እና ጫናዎች ለመንግስት ወይም ለገዢው ፓርቲ ብቻ የሚተው እንዳልሆኑ እና ሁሉም በመተባበር መቆም እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡

የራያ ራዩማ ፓርቲ የአመራር አባሏ ሸዋዬ በሪሁን ÷ ሀገርን ከፖለቲካ ልዩነት ባሻገር ማሰብና በጋራ መቆም የተገባ እንደሆነ ነው ያብራሩት፡፡

የኢትዮጵያ ሴት ፖለቲከኞች ጥምረት አመራር አባሏ ነቢሃ መሀመድ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የራሷን ችግር የመፍታት አቅም እንዳላት በማንሳት የማንንም ጣልቃ ገብነት አትሻም ብለዋል፡፡

ፖለቲከኞቹ ያለልዩነት በጋራ በመቆም እውነታውን በማስረዳት፣ መረጃዎችን በማቅረብ እና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የጋራ ሥራዎች እንዲሰሩም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.