Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ህዝብ የሽብር ቡድኑን የግፍ አገዛዝ ለመጨረሻ ጊዜ በቃህ የሚልበት ጊዜ አሁን ነው – የፓለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ህዝብ የሽብር ቡድኑን ሕወሓት የግፍ አገዛዝ ለመጨረሻ ጊዜ በቃህ የሚልበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የፓለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን ገለጹ፡፡

የትግራይ ህዝብ አሁን ላይ ከመንግስት ጎን ቆሞ የሽብር ቡድኑን በቃህ የሚልበት ጊዜ መሆኑን የፖለቲካ ተመራማሪ የሆኑት አቶ በቀለ ሐብታሙ ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው የዘርፉ ተመራማሪ አቶ ኤርሚያሰ ታደሰ ደግሞ የትግራይ ህዝብ አሁን ላይ የተፈጠሩ ምቹ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ከመንግስት ጎን በመቆም የሽብር ቡድኑን የግፍ አገዛዝ ማስቆም ይገባዋል ብለዋል ፡፡

መንግስት ሰብዓዊ ድጋፍ እና መሰረተ ልማቶችን በማሟላት የትግራይ ህዝብ ከግፍ አገዛዝ ነጻ እንዲወጣ ማድረግ እንደሚገባውም አብራርተዋል ፡፡

ከሰሞኑ የተደረጉት የውጭ ያልተገባ ጣልቃ ገብነትንና ጫናን የተቃውሞ ሰልፎች ህዝባዊ አንድነት የተንጸባረቀባቸዉ እንደሆኑም ተንታኞቹ አስረድተዋል ፡፡

እነኝህ እንቅስቃሴዎች በሽብር ቡድኑ የግፍ አገዛዝ በጭቆና ቀንበር ውስጥ ስላለው የትግራይ ህዝብ ድምጽ እንደሆኑም የፓለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎቹ የሚነሱት ሃሳብ ነዉ ፡፡

የትግራይ ክልል ህዝብ ከአሸባሪ ቡድኑ የግፍ አገዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲላቀቅ የተጠናከሩ ሥራዎች ይጠበቃሉም ብለዋል፡፡

በአወል አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.