Fana: At a Speed of Life!

ላሊበላ ከተማ እና አካባቢዋ በድጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ የተቋረጠባቸው ላሊበላ፣ ላስታ ወረዳ እና ሙጃ ከተማ በድጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ፡፡
የኤሌክትሪክ ኃይሉን በድጋሚ ያገኙት በሽብር ቡድኑ ህወሓት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአላማጣ – ላሊበላ የ66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና መጠናቀቁን ተከትሎ ነው፡፡
የወልዲያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሽመልስ ወልደሰማያት እንደገለጹት÷ የጥገና ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅና አካባቢዎቹን በድጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የዲስትሪክቱ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል፡፡
በሰቆጣና አካባቢዋ የሚገኙ ከተሞች የተቋረጠባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል እዲያገኙ ይሠራልማለታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.