Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በቅርቡ የዓየር መቃወሚያ ሚሳኤሎቿን ወደ ዩክሬን ትልካለች – ፔንታጎን

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርብ ጊዜ ውስጥ አሜሪካ የመጀመሪያውን ዙር ሁለት የዓየር መቃወሚያ መሣሪያዎች ወደ ዩክሬን እንደምትልክ ገለጸች።

የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በገባችው ጦርነት ውስጥ ከሚፈጸምባት የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) እና ሚሳኤል ጥቃት ራሷን ትክላከል ዘንድ የዓየር መቃወሚያዎችን ለኪየቭ እሰጣለሁ ብሏል።

ሩሲያ በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎች በዩክሬን ወታደራዊ ዒላማዎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ኪየቭ የአጭር እና የመካከለኛ ርቀት የዓየር መቃወሚያዎችን ዋሺንግተን እንድትሰጣት ለሳምንታት ደጅ ስትጠና ቆይታለች፡፡

ይህን ተከትሎም የአሜሪካ የደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የሆኑት ጆን ኪርቢ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ÷ ፔንታጎን “ስምንት የአጭር እና የመካከለኛ ርቀት የዓየር መቃወሚያዎችን ከእነተተኳሾቻቸው ወደ ዩክሬን ለመላክ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡

ዩክሬን ከስምንቱ የዓየር መቃወሚያዎች መካከል ሁለቱን በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደምትረከብም ቃል መግባታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

እንደ ባለሥልጣኑ አሜሪካ መሬት ላይ የሚተከሉትን የዓየር መቃወሚያዎች ለዩክሬን የምትልከው ከመለዋወጫቸው ጋር ነው፡፡

ከዓየር መቃወሚያ ሚሳዔሎቹ ፣ መለዋወጮዎቻቸው እና ተተኳሾቻቸው በተጨማሪም ዩክሬን የተለያዩ ሰው አልባ የአየር ላይ መቃወሚያዎች እንደሚቀርብላትም ገልጸዋል፡፡

አሜሪካ ለዩክሬን የምትልከው የዓየር መቃወሚያ የሩሲያንም ሆነ ከማንኛውም ወገን ጥቃትሊያደርሱ የሚላኩ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የመምታት፣ የተተኮሱ ሚሳኤሎችን የማክሸፍ፣ እንዲሁም ተዋጊ አውሮፕላኖችን መትተው የመጣል አቅም አላቸው ተብሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.