Fana: At a Speed of Life!

ሁለቱ ኮሪያዎች ተኩስ ተለዋወጡ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ ተኩስ መለዋወጣቸው ተሰማ፡፡

ሁለቱ ሀገራት የተለዋወጧቸው የሚሳዔል ጥቃቶች ጉዳት ሳያደርሱ በባሕር ዳርቻዎቻቸው አቅራቢያ ማረፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አስቀድማ ሰሜን ኮሪያ የተኮሰችው ሚሳኤል ሶኮቾ በተሰኘችው የደቡብ ኮሪያ ከተማ አቅራቢያ በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ማረፉም ነው የተገለጸው፡፡

ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ በኩል ተፈጸመብኝ ላለችው ድፍረትም ከሦስት ሠዓታት ቆይታ በኋላ 3 ሚሳኤሎችን አከታትላ በማስወንጨፍ አጸፋውን መልሳለች፡፡

ደቡብ ኮሪያ ጥቃቱን “ተቀባይነት የሌለው” እና ሉዓላዊነቷን የጣሰ አድርጋ ልትወስደው እንደሚገባም አንድ የሀገሪቷ ወታደር ገልጿል፡፡

ሁለቱ ኮሪያዎች የተለዋወጧቸው የሚሳኤል ጥቃት ሙከራዎች በድንበሮቻቸው አቅራቢያ ማረፋቸው ነው የተሰማው፡፡

ሁለቱ ኮሪያዎች በድንበር ጉዳዮቻቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል፡፡

በተለይም ሰሜን ኮሪያ የድንበር ማካለሉን አትቀበልም ነው የተባለው፡፡

ሰሜን ኮሪያ ከአምስት ዓመታት ቆይታ በኋላ በቅርቡ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ለመጀመር ዝግጅቷን መጨረሷን የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ የሥለላ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.