Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ላልተወሰነ ጊዜ  የፓስፖርት አገልግሎት  መስጠት ማቆሙን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የፓስፖርት አገልግሎት  መስጠት ማቆሙን አስታውቋል።

የኤጀንው  የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተሬሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ድርጅቱ  ከዛሬ  ጀምሮ አዲስም ሆነ እድሳት ለሚያስፈልገው ፓስፖርት አገልግሎት አይሰጥም።

ይሁን እንጂ ቁልፍ ለሆኑት የመንግስት ስራዎች እና ለህመም ብቻ የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሰጥ መሆኑን የገለጹ,ት ዳያሬክተሩ፥ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳይበር በተወሰኑ 30 ሀገራት ተግባራዊ እንደማይሆን ጠቁመዋል።

ከዚህ ባለፈም  የኢ-ቪዛና ተደራሽ ኦን አራይቫል ቪዛም አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑንም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

በተጨማሪም የመኖሪያ ፈቃድ እና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ መስጠት መቋረጡን ገልጸዋል ።

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.