Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጎፋ ዞን ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጎፋ ዞን ጉብኝት አደረጉ።

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሳውላ እና አካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም ፥ ሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋን በየፈርጁ መታደሏን ከሚያሳዩን ሥፍራዎች አንዱ የጎፋ ዞን ነው ብለዋል።

ከዞኑ አልፎ ክልሉን ለማልማት የሚያስችል ያልተነካ ዐቅም አለው ያሉ ሲሆን ፥ ባለ ግርማ ሞገሱ ወይላ ተራራም በውስጡ የያዘው ብዝኃነት የሀገራችን የኢትዮጵያ ማሳያ ያደርገዋልም ነው ያሉት።

የዶጫ ደምበላ አርሶ አደሮች በ80 ሄክታር ላይ ያመረቱት ሰሊጥ፣ ማሾ፣ አኩሪ አተር፣ ጤፍ እና ፍራፍሬም አካባቢው የተፈጥሮ በረከት እንደተቸረው የሚያሳዩ እንደሆኑም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.