በሰሜን ዕዝ ላይ ሽብርተኛው ትህነግ የፈጸመው ጥቃት ነገ በድሬዳዋ ይታሰባል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ አሸባሪው ትህነግ የፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ ነገ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ይካሄዳል፡፡
የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሀር እንደገለጹት ÷ በሰሜን ዕዝ ላይ ሽብርተኛው ትህነግ የፈጸመውን ወንጀል በሚያወግዙና የሠራዊቱን ጀግንነት በሚያወድሱ መሰናዶዎች ዕለቱን ለማሰብ ዝግጅት ተደርጓል።
ጀግናው መከላከያ ሠራዊት ሉዓላዊነትን ለማስከበር ለሚከፍለው መስዋዕትነት ነዋሪው ያለውን ክብርና ደጀንነት በተለያዩ መንገዶች እየገለጸ ነው ማለታቸውን የአስተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
በነገው ዕለት ከሚኖረው የመታሰቢያ ዝግጅት ቀደም ብሎ ዛሬ አመሻሽ ላይ ጧፍ የማብራት እና የእግር ጉዞ እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡