ለሰሜኑ ግጭት ሰላማዊ እልባት ለመስጠት ሲደረግ የነበረው ንግግር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ እልባት ለመስጠት ሲደረግ የነበረው ንግግር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቀቀ።
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ሲቋጭ የተደረገው ስምምነት ግጭትን በዘላቂነት ማቆምን ያካተተ ነው።
በትግራይ ክልል ህገመንግስታዊ ስርዓት እንዲመለስም ከስምምነት ተደርሷል።
ስምምነቱ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችል የጠቀሰ ሲሆን፥ በዚህም መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱ ይሆናል።
በትግራይ ክልልም መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀመርም እንደዚሁ ከስምምነት ተደርሷል።