Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱ ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱንና ብሄራዊ ጥቅማችንን ባስከበረ መልኩ ተጠናቋል- ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱ ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱንና ብሄራዊ ጥቅማችንን ባስከበረ መልኩ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡

ዶክተር ለገሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ ስምምነቱ መንግስት ካስቀመጠው አቅጣጫ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመላ ህዝባችንን ፍላጎት የሚያሟላ፣ ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥና የትግራይን ህዝብ መሠረታዊ ችግሮች የሚፈታ ነውም ብለዋል፡፡

ወደዚህ ድል የደረስነው መላው የፀጥታና የደህንነት ሃይሎቻችን በከፈሉት መስዋእትነትና በመሬት ላይ ባስመዘገቡት ድል እንዲሁም ህዝባችን አንድ ሆኖ በመቆሙና መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ ባሳየው ቁርጠኝነት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ድሉ የመላ ኢትዮጵያውያን ድል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ አሸናፊዋ ኢትዮጵያ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.