የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያው ፕሬዚዳንት ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ ዕልባት ለመስጠት ስምምነት ላይ በመደረሱ ደስታቸውን ገለፁ

By ዮሐንስ ደርበው

November 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሳሞኢ ሩቶ ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ ዕልባት ለመስጠት ስምምነት ላይ በመደረሱ ደስታቸውን ገለፁ።

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአፍሪካ ኅብረት አመቻችነት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሲካሄድ በቆየው የሰላም ንግግር ውጤትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሲካሄድ በቆየው የሠላም ሂደት ላይ የተሳተፉትን ሁለቱን ወገኖች ያመሰገኑ ሲሆን፥ ስምምነት ላይ ደርሰው በዛሬው ዕለት በመፈራረማቸውም አመስግነዋል፡፡

ሠላም ለማስፈን ላደረጉት ጥረትም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመተሳሰብ ፣ የአንድነት እና የእርቅ ጊዜ እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል፡፡