Fana: At a Speed of Life!

በተደረሰው ስምምነት የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ደስታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መንግሥት እና ህወሓት ሰሞኑን ያካሄዱትን የሰላም ንግግር ተከትሎ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሸል ደስታቸውን ገለጹ፡፡

ቻርለስ ሚሸል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ሕብረት አወያይነት ለስምምነት በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

ዘላቂ ሰላምን ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ሰብዓዊ እርዳታን ለማረጋገጥ እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት ለመመለስ ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት በቀጣይ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ የአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔት ዌበር በተደረሰው ስምምነት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው÷ ስምምነቱን አበረታች እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ሁለቱም ወገኖች ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት አመስግነዋል፡፡

ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተግራዊ እርምጃ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.