Fana: At a Speed of Life!

አቶ መላኩ አለበል ካኪ የአይሱዙ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ካኪ የአይሱዙ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ስራ እያከናወነ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምራቾች መዳረሻቸውን ሩቅና ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪነት ላይ ትኩረት በማድረግ የስራ ውጤታቸው በጥራት፣በጊዜና በመጠን የተለካ እንዲሆን ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

እርስበርስ በመተሳሰር አንዱ ለአንዱ ግብዓት የሚያቀርብበትን ሂደት በመፍጠር የተጠናከረ ትስስራዊ የቅብብሎሽ የስራ ሂደትን በመከተልና ለሚያጋጥማቸው የግብዓት እጥረት መፍትሄ ማበጀት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት፡፡

አምራቾች ለቆሙለት አላማ ስኬት፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ የውጭ ምንዛሬን ማዳንና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ የዜግነት ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

እንደ ሀገር የተያዘውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር በማሳለጥ እምርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ የሰው ሀብት ልማት ላይ አበክረው መሥራት እዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.