Fana: At a Speed of Life!

ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ነጥቦች፡-

1. ስምምነቱ አንቀፅ 3 ላይ በተመለከተው መሠረት 10 ቀናት በፈጀው የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት ውይይት ሁለቱ ወገኖች ጦርነት ለማቆም እና ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ተስማምተዋል፡፡ ስምምነታቸውንም ለኢትዮጵያውያን እና ለመላው ዓለም ለማወጅ ተስማምተዋል፡፡

2. ሁለቱ ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ የዘለቀው የሁለት ዓመት ግጭት በዘላቂነት ለማቆም ተስማምተዋል፡፡

3. ግጭቱ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የኢትዮጵያውያንን ሕይወት የቀጠፈ እና በንብረት ላይም ውድመት ያስከተለ ሲሆን ይህንን የግጭት ምዕራፍ ዘግቶ በሰላምና በስምምነት መኖር የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም መሆኑ በስምምነቱ ተመልክቷል።

4. ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ እና ህገ መንግስቱን ለማስከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጥ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑ ተመልክቷል። ኢትዮጵያ አንድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ብቻ እንዳላትም ተገልጿል፡፡ ነባራዊ የጸጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትም የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ እንደሚፈቱ፣ ጦሩን የማፍረስ እና ከማህበረሰቡ ጋር ለመቀላቀልል መሥማማታቸውም ተመልክቷል፡፡

5. የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታ ለማድረስ ከሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በቁርጠኝነት ተባብሮ ለመሥራት ተስማምቷል፡፡

6. በትግራይ ክልል ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ወደ ቀድሞው ለመመለስ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት፣ የሽግግር የፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ ተጠያቂነትን፣ እውነትን እና እርቅን ለመተግበር ተስማምተዋል።

ይቀጥላል…

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.