Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ ሲጓዙ ህይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ ሲጓዙ ህይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ በጭነት መኪና ውስጥ ሲጓዙ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ህይወት ማለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “በርካታ ሰዎች ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ ሲጓዙ ህይወታቸው ማለፉን በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ሰምቻለሁ፤ ከእነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያውንያን እንደሚገኙም ተረድቻለሁ” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም የሟቾችን ማንነት እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ለማጣራት ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በኢትዮጵያውያን በዜጎች ላይ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ፤ ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

የሟቾቹን ብዛት እና መሰል ዝርዝር መረጃዎች በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የገለጸው ሚኒስቴሩ፥ በጉዳዩ ዙሪያ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በሞዛምቢክ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.