Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ በጋምቤላ ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች ተዘክሯል።
መታሰቢያው “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን÷ በጋምቤላ ከተማ ዐደባባይ የሻማ ማብራት ተከናውኗል፡፡
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ጁል ናንጋል የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ወክለው እንዳሉት ÷ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ኢትዮጵያን ሲጠብቅ በነበረው ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የደፈረ ነው።
ጥቃት የተፈጸመበት ዕዝ የአካባቢውን ማህበረሰብ በሥራ በመገዝ የሕዝብ አለኝታነቱን ሲያሳይ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡
የጋምቤላ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኡጁሉ ጊሎ በበኩላቸው÷ የሰሜን ዕዝ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከጀርባው መጠቃቱ አሳዛኝ ክስተት መሆኑንም ነው የገለጹት።
በክልሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ተወካይ ፒተር አማን እንደገለጹት ÷ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግሥትና የሀገርን ዳር ድንበር ከሚያስከብረው የመከላከያ ሠራዊት ጎን ነን፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.