የሀገር ውስጥ ዜና

ዛሬ ኢትዮጵያና ሰላም ድል አድርገዋል- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

By ዮሐንስ ደርበው

November 03, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የዛሬው ቀን ኢትዮጵያና ሰላም ድል ያደረጉበት ነው” ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

ኢትዮጵያን በመወከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተሰየመው ልዑክ አባል የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን “ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

አያይዘውም “እኔ ልገልጸው የማልችለው ደስታ ተሰምቶኛል” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ዛሬ ሰላምና ኢትዮጵያ ድል አግኝተዋልም ነው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን።

አምባሳደር ሬድዋን ወደፊት መጓዝና ብሩህ ነገር ለመፍጠር መስራት እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሓት መካከል ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያከበረና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስጠበቀ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!