የሀገር ውስጥ ዜና

በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ስኬት አሜሪካ ድጋፏን ትቀጥላለች- አንቶኒ ብሊንከን

By ዮሐንስ ደርበው

November 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ስኬት አሜሪካ ድጋፏን ትቀጥላለች ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ፡፡

በፕሪቶሪያ ሲካሔድ የቆየው የኢፌዴሪ መንግስትና ህወሓት የሰላም ውይይት በስኬት መጠናቀቁንም አድንቀዋል፡፡

አንቶኒ ብሊንከን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር በመተባበር መድረኩን በማዘጋጀቷ አመስግነዋል፡፡

የሰብዓዊ እርዳታና መልሶ መቋቋም ሥራን በተመለከተም አሜሪካ ከአፍሪካ ሕብረት ጎን በመሆን ድጋፏን እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!