የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ህብረት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል-ሙሳ ፋኪ ማህማት

By Melaku Gedif

November 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማህማት ሕብረቱ የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት ለደረሱበት የሰላም ስምምነት ዘላቂነት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ።

ኮሚሽነሩ በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት ሲካሄድ በነበረው የሰላም ውይይት የግጭት ማቆም ስምምነት ለተፈራረሙት ወገኖች አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ሕብረቱ መንግስትና ሕወሓት በደረሱበት ስምምነት መሰረት ዘላቂ ሰላምን እንዲያስቀጥሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

ትናንት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያከበረና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስጠበቀ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!