Fana: At a Speed of Life!

ጥቅምት 24 “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) ጥቅምት 24 “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሀሳብ እለቱን የሚያስታውስ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ጊቢ ውስጥ ተካሄደ።

በመታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ሰራተኞችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል።

ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ የዛሬው ቀን የተሰውትን የምንዘክርበት በግንባር የተዋደቁትንና ለዛሬው ድል ያበቁንን የምናስብበት ነው ብለዋል።

መከላከያችን የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዋስትና መሆኑን በመጥቀስም ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ጠብቃ እንድትቆይ መከላከያ ለከፈለው መስዋትነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጥቅምት 24 ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አንረሳውም እንዘክረዋለን ያሉት ምክትል ከንቲባው ፥ ኢትዮጵያ ዛሬም በሀገር ወዳድ ልጆቿ ሰንደቋ መውለብለቡን ይቀጥላልም ብለዋል።

 

በዘቢብ ተክላይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.