የጋሞ ዞን በተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብት የታደለ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋሞ ዞን በተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብት የታደለ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት ፥ የጋሞ ዞን ህዝብ በጠንካራ የሥራ ባህሉ አማካኝነት ልምላሜን ለትውልድ ማስተላለፍ ችሏል፡፡
የጋሞ ዞን በተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብት የታደለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የጋሞ ሕዝብ ሌላው መታወቂያው ሰላምና ዕርቅን ባህሉ ማድረጉ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
አክለውም ፥ አሁንም ለሰላም ላባችንን ብናፈስ፣ በጦርነት የወደሙብንን አካባቢዎች መልሶ ለመገንባት ካለን ላይ ብናዋጣ እናተርፋለን እንጂ አንጎዳምም።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!