Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ በሐረሪ ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ በሐረሪ ክልል ተካሂዷል፡፡
 
የመታሰቢያ መርሐ ግብሩ “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡
 
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ሱልጣን አብዱሰላም እንዳሉት ÷ በመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ አባላት ላይ የደረሰውን ጥቃት መቼም አንረሳውም።
 
የሰራዊት አባላት የከፈሉት መስዋዕትነት ለሀገር አንድነት፣ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ለብሔር ብሔረሰቦች መሆኑንም አንስተዋል፡፡
 
በመርሐ ግብሩ ላይ በየደረጃው የሚገኝ የክልሉ አመራሮችእና ሰራተኞች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የሀረሪ ክልል ፖሊስ አመራርና አባላት መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.