ቱርክ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት የተደረሰውን ሥምምነት አደነቀች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት የተሰማትን ደስታ ገለጸች።
የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ÷ በፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው ስምምነት እንዳስደሰተው ገልጿል፡፡
የተደረሰው ስምምነት ዘላቂ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለንም ነው ያለው ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡
የሰላም ውይይቱ እንዲካሄድ ጥረት ላደረጉ እና ላስተባበሩ አካላትም ምስጋናው አቅርቧል።
በኢትዮጵያ ለሚደረገው የሰላም ግንባታ ሂደት የቱርክ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!