Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ በአፋር ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ መርሐ ግብር በአፋር ክልል ተካሂዷል፡፡
 
መርሐ ግብሩ “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል ነው በተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደው፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የክልሉ አመራር አካዳሚ ኃላፊ አቶ ኢድሪስ መሀመድ ÷ ወደ ተሻለ የጋራ እድገት እና ሰላም ለመዝለቅ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
 
መከላከያ ሰራዊት የሀገር አለኝታ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ከሰራዊቱ ጎን እንዲቆምና ደጀንነነቱን አጠናክሮ እንደቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.