Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ”የሌማት ትሩፋት” መርሐ ግብርን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ”የሌማት ትሩፋት” የተሰኛ ሀገር አቀፍ የእንስሳት ተዋጽዖ ልማት መርሐ ግብርን አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ‘የሌማት ትሩፋት’ የልማት ዘመቻ ማስጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌማት÷ አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸው፥ በቂ እና አመርቂ ምግብ ለማግኘት እንዲቻል ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፥ በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት ዘመቻ በቤተሰብ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት ያፋጥናል ብለዋል፡፡

መርሐ ግብሩ ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚተገበር ሲሆን፥ ዋና ግቡም የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የምግብ ስርዓትን ማሻሻል ነው።

በተጨማሪም የሥራ ዕድል ፈጠራንና የወጪ ንግድ ገቢን ማሳደግ እንዲሁም ከውጭ የሚገባ የእንስሳት ተዋጽኦን በሀገር ውስጥ ለመተካት ያለመ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.