የሀገር ውስጥ ዜና

ሩሲያ የሰላም ስምምነቱ  ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት የሚጥል መሆኑን ገለጸች

By Melaku Gedif

November 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የፌዴራል መንግስትና ህወሓት የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት የሚጥል መሆኑን ገለጸች።

የሩሲያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ባወጣው መግለጫ ÷ በፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አድንቋል፡፡

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ  ሰላምና ብልጽግና ጠንካራ  መሰረት ከመጣሉ ባሻገር የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚያስችል ኤምባሲው አመላክቷል፡፡